Fana: At a Speed of Life!

የሰኔ 30 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በአርባ ምንጭ ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትምህርት ዘርፍ የሰኔ 30 አረንጓዴ አሻራ ቀን “ኢትዮጵያን እናልብስ”መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት በበአርባ ምንጭ ከተማ ችግኞችን በመትከል ተጀምሯል።

በመርሃ ግብሩ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የአስሩም ክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በተያዘው በጀት ዓመት በትምህርት ዘርፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ 500 ሚሊየን ያህል ችግኞቾ እንደሚተከሉ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል፡።

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፉ የትምህርት አመራርና ሠራተኞች መምህራንና ተማሪዎች ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ በሚደረገው” ኢትዮጵያን አናልብሣት” የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ አሻራቸውን እንዲያሳርፉም ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.