የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና የወጣችበት ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ ላደረጉ  የፖለቲካ ፓርቲዎች ምስጋና አቀረቡ

By Meseret Demissu

June 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና የወጣችበት ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ ላደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ÷ከስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ አንድ ሳምንት በኋላ ዛሬ ጠዋት ከፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝቼ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና የወጣችበት ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ ብለዋል፡፡

አያይዘውም  ገና በጅምር ላይ ያለውን ዴሞክራሲያችንን ለማጠናከር በምርጫ ሂደቱ ውስጥ የታዩ ተግዳሮቶች እና ክፍተቶችን በመገምገም ምን እንደተማርንባቸው ተወያይተናል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!