የሀገር ውስጥ ዜና

የጀነራል ሰዓረ መኮንንና የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሃውልት በቅርቡ ይመረቃል

By Tibebu Kebede

June 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንንና የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሃውልት ስራ መጠናቀቁን ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ “ወታደር ብሄር የለውም” በሚል ንግግራቸው የሚታወቁት የጀነራል ሰዓረ መኮንን እና የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሃውልት ስራ ማጠናቀቁን ወይዘሮ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ሃውልቱ በቅርቡ ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት እንደሚመረቅም ምክትል ከንቲባዋ ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!