የሀገር ውስጥ ዜና

ከየክልሎቹ የሚሰበሰቡ የምርጫ ድምጽ ውጤቶች ርክክብና ጉብኝት ተደረገ

By Tibebu Kebede

June 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከየክልሎቹ የሚሰበሰቡ የምርጫ ድምጽ ውጤቶች ርክክብና ጉብኝት ተደረገ።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው የመገናኛ ብዙሀን ጉብኝት በአጠቃላይ ከየምርጫ ክልሎች ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚመጡ የምርጫ ውጤቶች ርክክብ ሒደት እና በአሁኑ ሰአት የውጤት አሰባሰብ ሒደቱ ተጎብኝቷል።

በመረጃ ርክክቡም የሚጠበቁ መስፈርቶችን መሠረት በማድረግ ከየምርጫ ክልሎች በሚጠበቀው መልኩ መሆኑ እየተረጋገጠ ርክክብ ተደርጓል።

378 የምርጫ ክልሎችም የምርጫ ውጤት አስረክበው የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው፡፡

በጉዳዩ ዙሪያም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ሶሊያና ሽመልስ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የየምርጫ ክልሎች ሀላፊዎች የውጤት ሰነዶችን በጸጥታ ሀይል ታጅበው እያስረከቡ መሆኑን ተናግረዋል።

በለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!