Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ::

ድጋፉ ኮሚቴው በጃፓን ቶኪዮ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለሚያደርገው ዝግጅት የሚረዳ መሆኑን የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ድጋፉን ለኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ አስረክበዋል፡፡

አቶ አቤ ሳኖ ከፍተኛ ወጪ ለሚጠይቀው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ባንኩ ያሳየውን ተነሳሽነትና ያደረገውን ድጋፍ ሌሎችም እንደሚከተሉት ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡

ባንኩ ስፖርቱን ለማሳደግ ጥረት ከሚያደርጉ ቀዳሚ የንግድ ድርጅቶች መካከል እንደሚመደብ የገለፁት ፕሬዚዳንቱ፥ የባንኩ ስፖርት ማህበር በእግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ እና በሌሎች የስፖርት አይነቶች በመሳተፍ ውጤታማ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ባንኩ ካደረገው የገንዘብ ልገሳ በተጨማሪ ህብረተሰቡም ለኦሊምፒክ ዝግጅቱ የበኩሉን መወጣት እንዲችል በሞባይል ባንክ አገልግሎትና በሲቢኢ ብር አማካኝነት የገንዘብ ልገሳ ማድረግ የሚያስችለውን አሠራር መጀመሩን አቶ አቤ ይፋ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው ባንኩ ያደረገው ድጋፍ አርያነቱ እጅግ የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም በኮሚቴው ስም የተሰማቸውን አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.