Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት የጆርዳን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት በኢትዮጵያ የጆርዳን አምባሳደር ዋፊ አያድ ጋር ተወያዩ፡፡

በወቅቱም አቶ ደመቀ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው ግንኙነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረና ታሪካዊ መሆኑን ጠቅሰው፥ ሃገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

አያያዘውም ተሰናባቹ አምባሳደር ግንኙነቱን ለማጠናከር ላበረከቱት አዎንታዊ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ደመቀ ሃገራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ በተለይም በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ፣ በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር እንዲሁም የትግራይን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለአምባሳደሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከዚህ ባለፈም የታላቁ ኢትዮጵያ ህደሴ ግድብን በተመለከተ በአረብ ሊግ በኩል የተያዘውን ፍትሃዊ ያልሆነ አቋም በተለመከተ ያላቸውን ቅሬታ ገልጸዋል።

ናይል የሁሉም የተፋሰሱ ሃገራት የጋራ ሀብት መሆኑን በመጥቀስም ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ህግን መሰረት በማድረግ ግድቡን እንደምትገነባ አስረድተዋል።

አምባሳደር ዋፊ አያድ በበኩላቸው በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ለማጠናከር በተደረጉ እንቅስቃሴዎች አዎንታዊ ውጤት መገኙቱን ጠቅሰው፥ በቀጣይም ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር የኢትየጵያ አየር መንገድ ወደ ጆርዳን የቀጥታ በረራ ቢጀምር አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን አውስተዋል።

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ በነበራቸው የስራ ቆይታ በመንግስት በኩል ለተደረገላቸው ድጋፍ እና ትብብር ምስጋና ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.