Fana: At a Speed of Life!

የላፕሴት ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ እና አላማ ለማስፈጸም የሚያግዝ የፊርማ ስነስርዓት ተከናወነ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን በጋራ የሚያለሟቸው የላፕሴት ፕሮጀክቶችን በተሳካ ለማከናወን የሚያስችል የባለሙያውዎች ኮሚቴ ምስረታ እና ፕሮጀቶቹን በተያዘላቸው ጊዜ እና አላማ ለማስፈጸም የሚያግዝ የፊርማ ስነስርዓት ተከናወነ።

ፕሮጀክቱን በሚመለከት የሃገራቱ የትራንስፖርት ሚኒስትሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ውይይት ተካሂዷል።

በዚህ ወቅትም ለፕሮጀክቶች አተገባበር የሚረዳና ከሃገራቱ የተውጣጣ የባለሙያዎች ኮሚቴ ምስረታም ተካሂዷል፡፡

የላፕሴት ፕሮጀክት በፍጥነት መንገድ፣ ባቡርና ሌሎች ግዙፍ መሰረተ ልማቶች አማካኝነት ሶስቱን ሀገራት የማስተሳሰር ውጥን የያዘ ነው።

ፕሮጀክቱ በፈረንጆቹ 2012 በሶስቱ ሃገራት መሪዎች የጋራ ስምምነት ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑ ይታወሳል።

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.