የሀገር ውስጥ ዜና

መከላከያ ሚኒስቴር በብር ሸለቆ ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች እያስመረቀ ነው

By Tibebu Kebede

June 29, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት በብር ሸለቆ ለ33ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች እያስመረቀ ነው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰው ሃብት ልማት ዘርፍ ዋና ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል ሐጫሉ ሸለመ፣ የምድር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ምክትል አዛዥ ለሰው ሀብት ልማት ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳንን ጨምሮ ከፍተኛ ጄኔራል መኮንኖች ተገኝተዋል።

የሀገር ኩራት፣ የወገን ጠበቃ፣ የራስን ሕይወት ትተው ለውድ ሀገራቸው ፅኑ ቃል ኪዳን ያሰሩት ምልምል ወታደሮች በብር ሸለቆ አደራ በመቀበል ላይ ናቸው፡፡

ተመራቂዎቹ ከመደበኛው ሰራዊት ጋር በመቀላቀል ከውስጥና ከውጭ የሚቃጣን ወረራ በመመከት እንዲሁም የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክው ያስቀጥላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!