Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ  አልበም ምርቃትና የሙት ዓመት መታሰቢያ  ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሶስተኛ የዘፈን አልበም ምርቃትና የአንደኛ ዓመት ሙት ዓመት መታሰቢያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በተለያየ ዝግጅት በታጀበው መርሃ-ግብር ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን ታድመዋል።

አርቲስት ሀጫሉ  ሁንዴሳ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር መጨረሻ በአዲስ አበባ ግዲያ እንደተፈጸመበት ይታወቃል።

አርቲስቱ በህይወት እያለ ያዘጋጀው ሶስተኛው የዘፈን አልበም÷ ‘ማል መሊሳ’ በሚል ርዕስ ታትሞ ለአድማጮች ቀርቧል።

የዘፈኑ 300 ሺህ ቅጂ በመጀመሪያ ዙር የተዘጋጀ ሲሆን÷ አልበሙም 14 ዘፈኖችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

ትናንት ምሽት በተካሄደ ፕሮግራም ለአርቲስቱ ሙት ዓመት መታሰቢያ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአርቲስቱ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ÷ ”ሀጫሉ በህይወት ቢለይም ትውስታውና ስራዎቹ ህያው ናቸው” ብለዋል።

ከአርቲስቱ ህልፈት ቦኃላ ከቤተሰቡ  ጎን ሆነው በተለያየ መልኩ ድጋፍ ላደረጉላቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም የአርቲስቱን ስም ባልተገባ መንገድ ለመጠቀም የሚፈልጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ወላጅ አባት አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ”ሀጫሉ የእኔ ብቻ ሳይሆን የመላው ኦሮሞ ህዝብ ልጅ ነው” ብለዋል።

”የልጄ ገዳዮች ህግ ፊት ቀርበው ፍትህ እንዲያገኙ ሁሉም እንደየ ሀይማኖቱ ጸሎት ያድርግልኝ” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በመርሃ-ግበሩ የጥበብ ስራዎችን የሚያግዝና በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ስም የተሰየመ  ፋውንዴሽን ተቋቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.