የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ ከፈረንሳይና ጣሊያን መንግስታት ጋር የተደረጉ የመከላከያ ስምምነቶችን አጸደቀ

By Tibebu Kebede

June 29, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፈረንሳይና ከጣሊያን መንግስታት ጋር የተደረጉ የመከላከያ ስምምነቶችን አጸደቀ።

ምክር ቤቱ እያካሄደ በሚገኘው 6ኛ ዓመት 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ከፈረንሳይ መንግስትና ከጣሊያን መንግስት ጋር የተደረገውን የመከላከያ ትብብር ስምምነት አስመልክቶ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጌታቸው ሃይለማርያም እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ብርቱካን አያኖ ስለስምምነቶቹ ጠቀሜታ አስረድተዋል።

በተጨማሪ ፓርላማው የፌዴራል ዋና ኦዲተር ያቀረበውን የተለያዩ ተቋማትን የ2012 በጀት ዓመት የሒሳብ ኦዲት ግኝት ሪፖርት እያዳመጠ መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!