ስፓርት

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያውን እሁድ ያደርጋል

By Tibebu Kebede

January 24, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለህንዱ የታዳጊዎች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን የፊታችን እሁድ ያከናውናል።

ብሄራዊ ቡድኑ በአሰልጣኝ ሳሙኤል አበራ እየተመራ ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ በባህር ዳር ልምምዱን እያከናወነ ይገኛል።

ጨዋታው እሁድ 9 ሰዓት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም ይደረጋል።

ከ15 ቀናት በፊት ካምፓላ ላይ በተደረገው የቅድመ ማጣሪያ መጀመሪያ ዙር ጨዋታ ዩጋንዳ 2 ለ 0 ማሸነፏ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ