Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን 14 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በማዕከላዊ ጎንደር ዞን 14 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ ነው።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ነጋ ይስማው ወቅታዊ የግብርና ስራዎችን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ÷  በዞኑ በ2013/ 2014 የምርት ዘመን 14 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሰራ ነው ብለዋል።

አቶ ነጋ ይስማው  አያይዘውም 480 ሺህ 495 ሄክታር መሬትን በሰብል ለመሸፈን መታቀዱን  ተናግረዋል።

በዚህም ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የእርሻ መሬት ሁለተኛ ዙር የታረሰ ሲሆን ሰላሳ በመቶ እስከአሁን በዘር ተሸፍኗልም ነው ያሉት።

61ሺህ 382 ሄክታር መሬት በመስመር መዘራቱን የተናገሩት ሀላፊው አሲዳማ መሬትንም የማከም ስራ ተከናውኗል ብለዋል።

ዝናቡ ከመዘግየቱ ውጪ ጥሩ የሚባል ዝግጅት መደረጉን የገለፁት ሀላፊው÷ ጎን ለጎንም በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ28 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ጥረት እየተደረገ ነው።

በክብረወሰን ኑሩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.