Fana: At a Speed of Life!

አንጋፋ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን  እድገት ፍኖተ ካርታ ላይ መከሩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አንጋፋ ጋዜጠኞች   እና ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የእድገት የሃሳብ ፍኖተ ካርታ ላይ መክረዋል፡፡

የምክክር መድረኩ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።

ተሳታፊዎቹ መገናኛ ብዙኃን በአሁን ሰዓት በብዙ እድሎች የታጀበ  መሆኑን ጠቁመው ÷የህብረተሰቡን ስነ ልቦና እና በሃገሪቱ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በተቀናጀ መልኩ መስራት ላይ ትልቅ ክፍተት እንደሚታይ አንስተዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን  ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት መከበር ከተጀመረ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የተሻለ እና የሚያበረታታ ሥራ ለማከናወን ትጋት ማሳየታቸው የማይካድ ቢሆንም በሰላም ግንባታ፣ ተግባቦት፣ ዲሞክራሲን ከማዳበር አኳያ ዛሬም ብዙ እንደሚቀራቸ ው ዶክተር ንጉሴ ተፈራ  ገልጸዋል

ከ50 ዓመት በላይ በጋዜጠኝነት እና በዲፕሎማሲ ስራ ለይ ያገለገሉት አቶ ማዕረጉ በዛብህ÷ ከምዕራቡ ዓለም የተኮረጀ እና የሀገሪቱን ህዝቦች ባህል፣ ትውፊት እና ስነ ልቦና ያላከበረ አሰራር ውስጥ መዘፈቅ እንደ ቀላል መታለፍ ያለበት ጉዳይ አይደለም ሲሉ አንስተዋል።

አያዘውም  “የሌሎች ባህል ናፋቂነት በሚዲያዎች ይታያል”ሲሉም ገልጸዋል፡፡

የሸገር ኤፍ ኤም ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ መዓዛ ብሩ በበኩላቸው÷አሁን ላይ ያሉ ብዙ የፖለቲካ አንቂዎች ሚዲያው እንዲሆን የሚፈልጉት እና የሚዘውሩበት ሪዮት አለማዊ ሃሳብ ከገለልተኝነት መርህ አንፃር ምን ያክል  ያራምድናል የሚለውን ጥያቄ ማጤን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ለ19 ዓመታት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋዜጠኛ  ሆነው ያገለገሉት እና አሁን ላይ በኮሚዩኒቲ ዲቨሎፕመንት ስራ ላይ የተሰማሩት ወይዘሮ አባይነሽ ብሩ÷ የመገናኛ ብዙኃን የቋንቋ አጠቃቀም የማህበረሰብን ክብር ያልጠበቀ ከመሆኑም በላይ ለማሻሻል  ጥረት አለመደረጉ የሚያሳዝን ነው ማለታቸውን ከኢመብባ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.