Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝ እና ዩክሬን ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ ትናንት በተደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች እንግሊዝ እና ዩክሬን ድል ቀንቷቸዋል፡፡

እንግሊዝ ከጀርመን ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜው ተቀላቅላለች፡፡

የማሸነፊያ ግቦችን ራሂም ስተርሊንግ እና ሃሪ ኬን አስቆጥረዋል፡፡

ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ዩክሬን ስዊድንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሩብ ፍጻሜው ተፋላሚ መሆኗን አረጋግጣለች፡፡

መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቆ በተጨማሪ ሰዓት ዩክሬን አሸናፊ ሆናለች፡፡

ዚን ቼንኮ እና ዶቭቢክ ለዩክሬን የድል ግቦችን ሲያስቆጥሩ÷ ለስዊድን ደግሞ ፎርስ በርግ የማስተዛዘኛ ጎሏን አስቆሯል፡፡

ምንጭ÷ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.