ቢዝነስ

ጃይካ የኢትዮጵያ የቆዳ ምርቶች በአሜሪካ እና አውሮፓ ገበያ ያላቸውን ተቀባይነት ለመጨመር ድጋፍ እያደረገ ነው

By Tibebu Kebede

June 30, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ጃይካ) የኢትዮጵያ የቆዳ ምርቶች በአሜሪካ እና አውሮፓ ገበያ ያላቸውን ተቀባይነት ለመጨመር ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡

ለዚህ እንዲረዳም ለአንድ ጫማ ፋብሪካ እና አምስት የቆዳ ቦርሳ አምራቾች ቴክኒካዊ ድጋፍ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

ስልጠናው ፋብሪካዎቹ የምርቶቻቸውን ጥራትና ንድፍ ለማሳደግና ለማዘመን እንዲያስችላቸው ያለመ መሆኑን ከጃይካ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ይህም ፋብሪካዎቹ ምርቶቻቸው በአሜሪካና አውሮፓ ገበያ ያላቸውን ተፈላጊነት ለመጨመር የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!