Fana: At a Speed of Life!

በጭልጋ ከተማ እና አካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የሰላም ችግር እየተሻሻለ ነው-ኮማንድ ፖስቱ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጭልጋ ከተማ እና አካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የሰላም ችግር እየተሻሻለ መምጣቱን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አስታወቀ፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ከጭልጋ እና አካባቢው 10 ቀበሌ ከሃይማኖት አባቶች ፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ከወረዳና ቀበሌ አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮማንድ ፖስት አመራር ሌተናል ጀኔራል ይመር መኮንን፥ ለብዙ ዘመናት የኖረ የህዝብ አንድነትና ዝምድና ላይ ጥላሸት በመቀባት እና ግጭቶችን በማባባስ ማዕከላዊ ጎንደር ዞንን የሽብርተኞች አደባባይ በማድረግ የሀገርን ሰላም ለማሳጣት የሚንቀሳቀሱ የፀረ-ሰላም ሃይሎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

በሃይማኖት እና በብሄር ግጭት እንዲነሳ በማድረግ ተፈጥሮ የነበረው የሰላም መደፍረስ ችግር በኮማንድ ፖስቱ እና በህብረተሰቡ የጠነከረ ቅንጅት በየጊዜው መሻሻሎች እየተመዘገቡ እንደመጡ አስረድተዋል፡፡

የ33ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ደስታ ተመስገን በበኩላቸው፥ የተመዘገበውን ማህበራዊ እንቅስቃሴ እና ሰላም በቀጣይነት ለማረጋገጥ ህብረተሰብ እና የፀጥታ አካላት ይበልጥ ተባብረው መስራት አለባቸው ብለዋል፡

የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ፣ ሰላምን ለመጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ መዘጋጀታቸውን እና በህዝብ ውስጥ ሰላማዊ ሰው በመምሰል የሃሰት መረጃን በማሰራጨት ለግጭት የሚዳርጉ ወንጀለኞችን በመጠቆም ከኩማንድ ፖስቱ ጋር እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.