Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ለወጣቶች የተሰራጨው የተዘዋዋሪ ብድር ከእቅድ በታች ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት ዓመት ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ የተሰራጨው የተዘዋዋሪ ብድር ዝቅተኛ መሆኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ቴክኒክ ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት መመሪያ አስታውቋል።
ለ745 ወጣቶች በዞኑ 74 ሚሊየን 545 ሺህ 36 ብር የተዘዋዋሪ ብድር ለመስጠት ታቅዶ፥ ተደራሽ መሆን የቻለው ለ35 ወጣቶች 3 ሚሊየን 251 ሺህ 319 ብር ብቻ ነው፡፡
ብድር የማሰራጨት አፈፃፀሙ በዞኑ ዝቅተኛ ነው ያሉት የገቢያ ልማትና ግብይት ቡድን መሪው አቶ ጳውሎስ አስማረ፥ ምክንያቱ ደግሞ ወረዳዎች ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ለወጣቶች ብደር ከሰጡ በኋላ በጊዜው ማስመለስ ባለመቻላቸው እንደሆነ ገልፀዋል።
ምስራቅ በለሳና ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳዎች የተመደበላቸውን ብድር ለስራ ፈላጊ ወጣቶች በተገቢው መንገድ ያሰራጩ ወረዳዎች ተብለዋል።
የወረዳዎች ብደር የማስመለስ ምጣኔ 97 በመቶ የደረሰ ባለመሆኑ በአዲስ ተደራጅተው ብድር ለሚጠባበቁ ወጣቶች መልስ መሆን አልቻለም።
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.