Fana: At a Speed of Life!

ከመተከል ዞን ተፈናቅለው የነበሩ ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች በ4 ማዕከላት መኖር ጀምረዋል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመተከል ዞን ተፈናቅለው የነበሩ ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች ይኖሩበት ወደ ነበረው ወረዳ ማዕከላት መመለሳቸው ተገለፀ፡፡

ከመተከል ዞን ተፈናቅለው የነበሩ ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች ይኖሩበት ወደነበረው ወረዳ በተመረጡ ማዕከል መመለሳቸውን የሰላም ሚኒስቴር ድጋፍና ክትትል ቡድን አረጋግጧል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ከዞኑ ኮማንድ ፖስት፣ ከአማራ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ በመሆን ከተፈናቃዮች ጋር በአደረጉት ተደጋጋሚ ውይይት ተፈናቃዮች ወደ ተዘጋጁ ማዕከላት ተመልሰው አስፈላጊው ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

ተፈናቃዮች አሁን ላይ በአራት ማዕከላት ማለትም በዳንጉር፣ቡለን ፣ድባጤ እና ማንዱራ ወረዳ መኖር ጀምረዋል፡፡

ወደ ማዕከላቱ ለተመለሱ ዜጎችም የአካባቢው ነዋሪዎች ምግብና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ አቀባበል እንደተደረገላቸው ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.