500 ባለ ሁለት መቶ ሐሰተኛ የብር ኖት ይዘው የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ሐሰተኛ የብር ኖት ይዘው የተገኙ ሁለት ግለሰቦች በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ የኢንተለጀንስ ምክትል ዳይሬክቶሬት አባላት ባደረጉት ጠንካራ ክትትል በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ኮካ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ነው ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ያዋሉት፡፡
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከ500 (አምስት መቶ) ባለ ሁለት መቶ ሐሰተኛ የብር ኖት ጋር ነው፡፡
ፖሊስ በአሁኑ ጊዜ በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ እያካሄደ ሲሆን ህብረተሰቡ ማንኛውም የዚህ አይነት ህገ-ወጥ ተግባር ሲያጋጥመው ጥቆማዎችን ለህግ አስከባሪ አካላት በመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ፌዴራል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!