Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ከፍተኛ አመራር መድረክ በዲላ ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ከፍተኛ አመራር መድረክ በዲላ ከተማ ተጀመረ፡፡
በመድረኩ የደቡብ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ አስቴር ከፍታው ÷የደቡብ ብልፅግና ሴቶች ሊግ ሃላፊ ወይዘሮ ነኢማ ሙኒር እንዲሁም የደቡብ ብልፅግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ወይዘሮ ፀሀይ ወራሳ ተገኝተዋል፡፡
ክልል አቀፍ የሴቶች ሊግ ከፍተኛ አመራር መድረኩ 6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሴቶች ሚናን እና ክልላዊ የሴቶች አደረጃጀት የ12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም እንደሚገመግም ከደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.