Fana: At a Speed of Life!

የጤናው ዘርፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ”የጤናው ዘፍር በጎ ፈቃደኞች ተሳትፎ ለጤናማ ማህበረሰብ ”በሚል መሪ ቃል የጤናው ዘርፍ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀምሯል።

በበጋው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተለያዩ ዘርፎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩት የጤናው ዘርፍ በጎ ፈቃደኞች የክረምት መርሃግብሩም ዛሬ ተጀምሯል።

በበጋው መርሃግብር ጤና ተቋማትን ለተገልጋዮች ምቹ ለማድረግ የጤና ተቋማት እድሳት፣ የህክምና መሳሪያዎችን የመጠገን፣ የስልጠናና የአቅም ግንባታ መስጠት፣ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተጠቃሽ  መሆናቸው ተመላክቷል።

በክረምት መርሃ ግብሩም እነዚህንና መሰል አገልግሎቶችን በማጠናከርና ከ20 በላይ የሙያ ማህበራት ከዚህ ቀደም በተበታተነ መልኩ ሲሰጡ የነበሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ ይደረጋል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በስራው ልምድ ያላቸውና የጤና ባለሙያዎች የሙያ እገዛና ለጀማሪ የጤና ባለሙያዎች የስራ ልምድን የማካፈል ስራ ይሰራልም ነው የተባለው ።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አለምጸሃይ ጳውሎስ÷ የጤናው በጎ ፈቃደኞችን በማመስገን የጤና ሚኒስቴር ለበጎ ፈቃድ ትኩረት በመስጠት የጤና ዘርፍ የበጎ ፈቃድ መመሪያ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።

የጤና ሙያ ማህበራቱ የማህበራቱን አባላት አስተባብረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

በሃይማኖት ኢያሱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.