Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል 300 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሲዳማ ክልል ሶስተኛው ዙር ኢትዮጵያን እናልብሳት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በሶሬሳ ጉዱማሌ ፓርክ ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አበራ ቡኖ፣ የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ፣ የምዕራብ ጉጂ ፣ የወላይታና ሌሎች የደቡብ ክልል አጎራባች ዞኖች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አቶ ደስታ ሌዳሞ አለም በአየር ንብረት ለውጥ እየታመሰች መሆኑን አስታውሰው ይህም ለአርሶ አደሮች ምርታማነት እንቅፋት በመሆኑ ችግሩን ለመቀነስ የሚያስችል 300 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም በችግኝ ተከላው እያሳየን ያለው ትብብርና አብሮነት በሰላም ማስከበርና አንድነትን በማጎልበት ረገድ ሊኖረዉ ይገባል ብለዋል፡፡
የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳደሪ አቶ አበራ በበኩላቸው ችግኙን በጋራ ስንተክል ሰላምንም አብረን ተክለናል ብለዋል።
በመቅደስ አስፋው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.