Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በምርጫ ድምፅ የመስጠት ሂደት ጋር ተያይዞ  አቤቱታ ካቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ ድምፅ የመስጠት ሂደት ጋር ተያይዞ  አቤቱታ  ካቀረቡ  የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አደረገ።

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳና የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ውብሸት አየለ በተገኙበት የተከናወነው የምክክር መድረክ÷ በፓርቲዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን መፍትሔ ለመስጠት ቦርዱ በሚከተለው ሥርዓት ላይ ካለው ጊዜ አንጻር ፓርቲዎቹ ፈጣንና የተሻለ መፍትሔ ለማግኘት ይረዳል ያሏቸውን የማዳበሪያ ሃሳቦች እንዲያጋሩ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ  መሆኑ ተመላክቷል።

የቦርዱ የህግ ክፍል ሃላፊ አቤቱታዎች ሊኖራቸው የሚገባውን ቴክኒካል ይዘት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቦርዱ ከቀናት በፊት ፓለቲካ ፓርቲዎቹ አቤቱታዎቻቸውን የሚያቀርቡበትን የመረጃ አቀራረብ ቅደም ተከተል ገምግሞ የትኞቹ ጉዳዮች አቤቱታ የሚቀርብባቸው እንደሆኑ እንዲሁም በምን መንገድ መቅረብ እንዳለባቸው በይፋ መግለጹ ይታወቃል።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ  ቦርዱ አቤቱታዎችን ለማደራጀትና ፓርቲዎቹ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁትን የመፍትሔ ሃሳቦች ሥርዓቱን ተከትሎ አደራጅቶ ለቦርዱ የሚያቀርብ የሕግ ባለሞያዎች ቡድን እንዳቋቋመ ገልጸዋል።

ቅርታ አቅራቢ የፖለቲካ ፓርቲዎችም  አካሄዱን ይረዳል ያሉትን ተጨማሪ ሃሳብ እንዲያቀርቡ  ጠይቀዋል።

ተሣታፊዎቹ ቦርዱ በጉዳዩ ላይ የፓርቲዎቹን ሃሳብ ለመስማት መድረክ ማዘጋጀቱ፣ ከዚህ ቀደም በነበሩ ምርጫዎች ያልነበረ ተሞክሮ ነው በማለት ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው÷ ሂደቱን ያግዛል ያሉትን የተለያዩ የመፍትሔ ሃሳቦች አጋርተዋል።

በዚህም መሰረት ቦርዱ በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ያመቸው ዘንድ ተመሳሳይ ደረጃ ያለው የአቤቱታ ፎርም በማዘጋጀት እና የፓርቲዎችን አቤቱታ ከሚቀበሉ የህግ ባለሞያዎችን በማዘጋጀት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.