Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ያወጀውን የተናጥል የተኩስ አቁም እንደምትደግፍ ገለፀች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ሲራጅ ራሺድ በኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካና የአፍሪካ ሕብረት ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ጆርጅ ኦሪና ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ አምባሳደር ሲራጅ በትግራይ ክልል የታወጀው የተናጥል የተኩስ አቁምን ጨምሮ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል።
የታላቁ የህዳሴ ግድብን በሚመለከትም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር መቀጠል ያለበት መሆኑንና የአፍሪካ ችግር በአፍሪካውያን መፈታት እንዳለበት ገልጸዋል።
የኬንያ መንግስትም በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት የሚካሄደውን የሶስትዮሽ ድርድር እንዲደግፍ በውይይቱ ወቅት ተጠይቋል፡፡
አምባሳደር ጆርጅ ኦሪና በበኩላቸው ኬንያ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ያወጀውን የተናጥል የተኩስ አቁም እንደምትደግፍ መግለፃቸውን ከኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘም በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት የሚካሄደውን የሶስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ጠቅሰው ÷ የሁለትዮሽ ጉዳዮችን አጠናክረው በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.