የሀገር ውስጥ ዜና

ደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ውሳኔውን እንደምትደግፍ አስታወቀች

By Meseret Demissu

July 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ዴንግ ዳው ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

አምባሳደር ነቢል መንግሥት የተናጥል ተኩስ አቁም ውሳኔ ማሳለፉን በተመለከተ ለምክትል ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅት መንግሥት ከሰባት ወራት በፊት በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ ሲጀምር ያስቀመጣቸውን ግቦች ማሳካቱን ገልጸዋል።

ይሁንና በክልሉ እየታየ ያለውን የሰብዓዊ ችግር ለማቃለልና አርሶ አደሩ የክረምቱን የእርሻ ወቅት እንዲጠቀም በማሰብ ውሳኔው መተላለፉን ተናግረዋል።

ዴንግ ዳውም  መንግሥት የተኩስ አቁም መወሰኑ በጎ እርምጃ መሆኑን ገልጸው÷ ደቡብ ሱዳን ሁልጊዜም ቢሆን ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!