የሀገር ውስጥ ዜና

በቡራዩ ከተማ  ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ

By Meseret Demissu

July 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቡራዩ ከተማ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ መያዙን የቡራዩ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ የጦር መሳሪያ ከህብረተሰቡ በደረሳቸው ጥቆማ መያዛቸውን የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር  ተሬሳ ካሳ አስታውቀዋል።

በዚህም 42 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦችና ከ 2 ሺህ 500 በላይ የተለያዩ ጥይቶችን ከሽንኩርት ጋር ተተቀላቅለው መያዛቸውን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ከዚሁ የወንጀል ድርጊት ጋር በተገናኘ  ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ ከቡራዩ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!