Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በተመለከተ ከተለያዩ አካላት ጋር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዎቹ አመራሮችና ከዓለም አቀፍ ተራድኦ ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራበት እንደሚገኝ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በተደረገው ጥረትም የዩኒቨርሲቲዎችን አመራር ለማግኘት የተቻለ ሲሆን ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ያሉም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
ስለሆነም የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸው በመልካም ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ተረድተው በመንግስት የተጀመሩ ጥረቶችን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በቀጣይ ተማሪዎች ፈተና ወስደው ሲጨርሱ የሚኖሩ ጉዳዮችን የሚያሳውቅ መሆኑ መገለፁን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወላጆችም በመደበኛ መገናኛ ብዙኃን የሚተላለፉ መረጃዎችን ብቻ እንዲጠቀሙና ተረጋግተው እንዲጠብቁ አሳስቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.