የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

By Tibebu Kebede

July 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎችእ ከፈተና በኋላ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

ተማሪዎቹ በትምህርት ቤቶቻቸው አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ማካሄዳቸውን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተማሪዎቹ ላደረጉት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ምስጋና አቅርበዋል።

ተማሪዎች አረንጓዴ አሻራ ማኖራቸውን የጠቀሱት ምክትል ከንቲባዋ ፥ መልካም ትውልድ እንዲህ እየተገነባ ይሄዳል ብለዋል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!