Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ለቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በራሳቸው እና በብልጽግና ፓርቲ ስም ነው ለቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

ፓርቲው ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ከ100 ዓመት በፊት የጀመረው ስራ በጠንካራ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አመራሮች አማካኝነት አሁን ላይ ትክክለኛው መስመር ላይ መሆኑን በመልዕክታቸው አንስተዋል፡፡

በእነዚህ ቁርጠኛ አመራሮች የተወጠነው ሀገራዊ ራዕም በቻይና ስር ሰዶ የነበረውን ድህነት በመቀነስ የዜጎችን ህይወት በእጅጉ ማሻሻል መቻሉን ነው የገለጹት፡፡

ፓርቲው የመጣበት መንገድ እና አሁን ላይ ያስመዘገበው እድገትና ውጤታማነትም በግላቸው መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው አውስተዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱአለምም ለቻይናው ኮሙዩኒስት ፓርቲ 100ኛ አመት የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.