Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 18ኛ ዙር መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ።

በመቐለ ከተማ ምክር ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ያለው ጉባዔ ለቀጣዮቹ አምስት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ የክልሉ ሥራ አስፈጻሚ አካላትን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸምን ጨምሮ በ21 ረቂቅ ዓዋጆችና ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ከእነዚህ መካከል ዳግም ወረዳዎችን ለማደራጀት የወጣውን ረቂቅ ዓዋጅ ጨምሮ፥ የከተሞችና የወረዳዎች የስራ አፈጻጸምን፣ የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ረቂቅ ዓዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅም ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ላይም ውይይት ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.