Fana: At a Speed of Life!

“የኢትዮጵያ ቅምሻ ” ፌስቲቫል በጂቡቲ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የኢትዮጵያ ቅምሻ ” ፌስቲቫል በጂቡቲ መካሄድ ጀምሯል።

ፌስቲቫሉን የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ካሳው እና የጂቡቲ ንግድና ቱሪዝም ሚኒስትር ሞሃመድ ዋርሳም በጋራ ከፍተዋል።

በፌስቲቫሉ የኢትዮጵያን ጣዕም የሚያሳዩ ምግቦችና መጠጦች፣ አልባሳትና የሙዚቃ ትዕይንት ለእይታ ቀርቧል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ካሳው ሁነቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከማጠናከር በዘለለ የኢትዮጵያን ብዝሃነት ለማሳየት የሚረዳ ነው ብለዋል።

የጅቡቲ ንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር የሱፍ ሙሳ በበኩላቸው፥ በቱሪዝም ዘርፍ በንግድ የተሰማሩ ድርጅቶች በፌስቲቫሉ በመሳተፍ እራሳቸውን እያስተዋወቁ በመሆኑ “የኢትዮጵያ ቅምሻ”’ መርሃ ግብር ለንግዱ ማህበረሰብም ተጨማሪ እድል የያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“የኢትዮጵያ ቅምሻ” ፌስቲቫል አዘጋጅ የኑሞንዶ ኢቨንትስ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ መሰለ፥ ፌስቲቫሉ ኮቪድ19 ያቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃትና የኢትዮጵያን ብዝሃነት ለማሳየት ጎብኚዎች እንዲመጡ መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ወዳሉበት መሄድ እንደሚገባ ማሳያ እንዲሆን ታስቦ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

“የኢትዮጵያ ቅምሻ” ፌስቲቫል ለሁለት ቀናት የሚቆይ ነው።

በመታገስ አየልኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.