ቢዝነስ

የልዩ ጣዕም ቡና የቅምሻ ውድድር አሸናፊ ቡናዎች የቅምሻና የማስተዋወቅ ስነስርዓት ተካሄደ

By Tibebu Kebede

July 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የልዩ ጣዕም ቡና የቅምሻ ውድድር ከ1 እስከ 5 ደረጃ የወጡ አሸናፊ ቡናዎች የቅምሻና የማስተዋወቅ ስነስርዓት ተካሂዷል።

ዝግጅቱ የፕሬዚዴንሺያል አዋርድ አሸናፊ ቡናዎችን ለዓለም አቀፍ ገዥዎች ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ እንዲሁም የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላን ጨምሮ የቡና ማህበራት ኃላፊዎች፣ የኤምባሲ ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ታዳሚዎች በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል።

በዘንድሮው የልዩ ጣዕም የቡና ውድድር እስከ 39ኛ ደረጃ ያገኙ ቡናዎች ዓለም አቀፍ ጨረታና ሽያጭ የፊታችን ረቡዕ እንደሚከናወን ኢቢሲ ዘግቧል።

እስካሁንም ከተለያዩ ሀገራት 180 ዓለም አቀፍ ገዢዎች በጨረታው ለመሳተፍ ተመዝግበዋል ነው የተባለው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!