Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ሊያከብር ይገባል-ቻይና

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ሊያከብር እንደሚገባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቻይና መልዕክተኛ አሳሰቡ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ትናንት ማምሻው ስብሰባ አድርጓል፡፡

በስብሰባው የተሳተፉት በተመድ የቻይና መልዕክተኛ ዳይ ቢንግ÷ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ሊያከብር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ የተኩስ አቁም እንደሚደረግ እምነታቸው መሆኑንም ነው መልዕክተኛው የገለጹት፡፡

ቻይና በክልሉ የተፈጠሩ ልዩነቶችን የሚመለከታቸው አካላት በውይይት እንዲፈቱ ድጋፍ እንደምታደርግም ተናግረዋል፡፡

የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል መንግስት የወሰደውን የተኩስ አቁም በማድነቅ እርምጃው በክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ከማገዝ አንጻር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.