Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የ2013 በጀት አፈፃፀም ሪፖርትን እያዳመጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት የ2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርትን እያዳመጠ ነው፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ÷ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን 1 ነጥብ 2 ሚሊየን የአፈር ማዳበሪያና 7ዐዐ ሺህ ዪሪያ በድምሩ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ማዳበሪያ ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል።

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ከ10 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ መልማቱን አቶ ርስቱ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።

በተጨማሪ በዶሮ እርባታ 6 ሚሊየን የአንድ ቀን ጫጩት ማቅረብ የተቻለ ሲሆን÷ 33 ሺህ ቶን ማር ማግኘት መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርም ክልሉ በዓመቱ 1 ነጥብ 57 ቢሊየን ችግኞችን ለማዘጋጀት አቅዶ አሁን ላይ 1 ነጥብ 34 ቢሊየን ችግኞች ዝግጁ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ ውስጥም እስካሁን 95 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ በስራ እድል የፈጠራ በርካታ ወጣቶች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን አንስተዋል፡፡

ለዚህም ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብድር ማሠራጨት ተችሏል ነው የተባለው፡፡

በክልሉ መኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታትና ማህበረሰቡን የቤት ባለቤት ለማድረግ 18 ሺ ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ የ16 ሺህ ቤቶችን ግንባት ማስጀመር መቻሉም በመልካም አፈጻጸም ተነስቷል።

በክልሉ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ቶሎ ለማጠናቀቅ በተሰራው ስራም ለመገንባት ከታቀደው 589 የውሃ ፕሮጀክቶች 178ቱን አጠናቅቆ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውሉ ተደርጓል።

ምክር ቤቱ በከሰዓት ውሎው በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በጥላሁን ይልማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.