Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር የአቅመ ደካሞችን ቤት ዕድሳት መርሃ ግብር አስጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር የሀገር አቀፍ በጎ አድራጎት እንቅስቃሴ አካል በመሆን የአቅመ ደካሞችን ቤት ዕድሳት በይፋ አስጀምሯል፡፡

ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት የሚገኙ አቅመ ደካሞችን ቤት ነው የማደስ ስራ ያስጀመረው፡፡

በመርሃ ግብሩ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰን ጨምሮ የሚኒስቴሩና የልደታ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ÷ በዚህም የ15 ቤቶችን እድሳት አስጀምረዋል።

እድሳቱ የሚከናወንላቸው ነዋሪዎችም አቅመ ደካማ ከመሆናቸው ባለፈ ከፍተኛ የጤና እክል ያለባቸው መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እድሳቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት÷የአቅመ ደካሞችን ቤቶች የማደሱ ስራ አቅም በፈቀደ መጠን ከክፍለ ከተማው ጋር በቅንጅት በመሆን የሚቀጥል ነው ብለዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ሽታዬ መሃመድ በበኩላቸው÷ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጤና ዘርፍ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር እንዲህ ባለው የበጎ ፈቃድ ስራ መሳተፉ የሚያስመሰግን መሆኑን አውስተዋል፡፡

በሜሮን ፈለቀ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.