Fana: At a Speed of Life!

ሰራዊቱ ለመላው የሀገሪቱ ህዝቦች የሚያገለግል እንጂ ለአንድ ወገን የቆመ አይደለም – ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ለመላው የሀገሪቱ ህዝቦች የሚያገለግል እንጂ ለአንድ ወገን የቆመ አለመሆኑን ሌተና ጄኔራል ባጫ ደበሌ ገልጸዋል፡፡

የሜጀር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 265 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የመከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተና ጄኔራል ባጫ ደበሌ÷ ሰራዊቱ ለህዝቡ የሚሰስተው ነገር እንደሌለና ተመራቂዎችም በሚሰማሩበት ስራ የሰራዊቱን ዕሴት ተላብሰው ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ከተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ ሰላሳ አንዱ ሴቶች ሲሆኑ÷ አስራ ሁለቱ የሶማሊላንድ ወታደሮች መሆናቸው ተገልጿል።

ኮሌጁ ከጀርመን ኤምባሲ ጋር በመተባበር የገነባቸውን የማስፋፊያ ወርክ ሾፖች እንግዶች ተዟዙረው መጎብኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዝግጅቱ ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ፣ የተለያዩ ሀገር አታሼዎች ፣ የሆለታ ከተማ ከንቲባና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.