Fana: At a Speed of Life!

የበጎ አድራጎት ስራ ለኦሮሞ ህዝብ ትውፊቱ ነው – ወ/ሮ ሰዓዳ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የበጎ አድራጎት ስራ ለኦሮሞ ህዝብ ትውፊቱ ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሰዓዳ ኡስማን።

የ2013 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት ስራ በኦሮሚያ ሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ “የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለሀገር ግንባታ “በሚል መሪ ቃል በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ በሻሻ ከተማ ተጀምሯል።

ወ/ሮ ሰአዳ ኡስማን በመላ ኦሮሚያ በዛሬው ዕለት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሴቶች የበጎ አድራጎት ስራ ላይ እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡
በዘመቻው ከ10 ሚሊየን በላይ ሴቶችና ወጣቶችን በማሳተፍ ከ20 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዷልም ነው ያሉት፡፡

ለዚህ ስራ ከበርካታ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የአቅመ ደካማ ቤቶችን መስራትና ማደስ፣ደም መለገስ፣ የህዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ የቦንድ ግዢ እና 3ሺህ አብዲ ቦሩ የመዋለ ህፃናት ትምህርት ቤቶች እነደሚሰሩን ጠቁመዋል፡፡

ህብረተሰቡም የጀመረውን መልካም ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ በበኩላቸው ÷ በዞኑ እስካሁን ድረስ በተሰሩ የበጎ አድራጎት ስራዎች የህብረተሰቡን ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮች መፍታት መቻሉን ገልፀዋል።

በዘንድሮው የክረምት በጎ አድራጎት ስራ ከ4 ሺህ በላይ የአቅመ ደካሞችን ቤቶች የመጠገን ፣ችግኝ መትከል ፣5 ሺህ ዩኒት ደም ለመለገስ እና 569 ቡኡረ ቦሩ ትምህርት ቤቶችን ለመስራት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

በተስፋሁን ከበደ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.