Fana: At a Speed of Life!

ፕላንና ልማት ኮሚሽን በቢሾፍቱ  ችግኝ ተከላ እና  በአየር ኃይልን ጎበኝት አካሄደ

 

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕላንና ልማት ኮሚሽን በቢሾፍቱ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እና በኢትዮጵያ አየር ኃይል ጉብኝት አካሄደ፡፡

የፕላንና ልማት ኮሚሽነር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ፣ የኮሚሽኑ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ ባለሞያዎች የተገኙበት በቢሾፍቱ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በማካሄድ በከተማው የሚገኘውን የኢፌዴሪ የአየር  ኃይልን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ የተመራው የአስጎብኚ ቡድን፣ የአብራሪዎች ዘመናዊ ት/ቤት፤ የአውሮፕላን መጠገኛ እና ሌሎች ክፍሎችን አስጎብኝተው ሁሉም አካላት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

ከጉብኝቱ በኋላ ክሚሽነር ፍፁም አሰፋ  እንዳሉት፣ ጉብኝቱ እጅግ አስደሳች እና በሀገራችን እንድንኮራ ያደረገ፣ ለሰራተኞቻችንም ጥሩ መነሳሳትን የፈጠረ እንደሆነ ጠቅሰው ስለ አጠቃላይ ጉብኝቱ አየር ሃይልን አመስግነዋል።

በተጨማሪም በዕለቱም ዓመታዊ የሰራተኞች ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን፣ በየዘርፉ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች እና በተካሄዱ ለውጦች ላይ ሰፋ ያለ ሪፖርት ቀርቧል፡፡

ማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ የተሰሩ ከተጠሪ ተቋማት ጋር የነበራቸውንም በመናበብ እና በጋራ የመስራት አግባብነት እንደሆነ በሪፖርቱ ተዳሷል።

 

ክትትልና ግምገማ  ከግልፅኝነትና ተጠያቂነት ጋር ተያይዞ የነበሩት ችግሮች ለመፍታት ታቅዶ እና ፈፃሚ አካላት ምን ምን መስራት እንዳለባቸው ግንዛቤ ተሰጥቶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፣ ረጅም ግዜን የፈጀ የዲጂታል ክትትልና ግምገማ ስርዓትን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሰርዓቱን የማበልፀግ ተግባር ተካሂዶ ወደ ስራ መገባቱን ከፕላንና ልማት ኮምሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.