የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባውን ነገ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባውን ነገ ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ያካሂዳል፡፡
ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የሚያካሂድ ሲሆን፤ የፌዴራል መንግስትን የ2014 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቀው ይጠበቃል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!