Fana: At a Speed of Life!

32 ኩንታል  ሀሺሽ  ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በሳንጃ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ መቆጣጠሪያ ጣቢያ 32 ኩንታል  ሀሺሽ ተብሎ የሚጠራው አድንዛዥ ዕፅ ተያዘ።

የጉሙሩክ ፈታሽ በለሙያ አበበ ተሜ አንደገለፁት መነሻውን ከምራዕብ ጎጃም አዴት ከተማ ወደ አብራጅራ ከተማ ለማለፍ ባደረገ ኮድ-3 አ አ A00925 አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ጤፍ ነው የጫንኩ በማለት የንግድ ፍቃድ በማሳየት ከጤፉ በታች በማድረግ ይዞ ለማለፍ ሲሞክር መያዙን ገልፀዋል።

አሽከርካሪውና ረዳቱ ለጊዜው በመሰወር እንዳመለጡም ገልፀዋል።

ኮትሮባንድ እንቅስቃሴና ህገ ወጥ ንግድ ላይ ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት የጉሙሩክ ባለሙያው፥ ህገ ወጦች ከእንዲህ አይነት እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡና ህብረተሰቡም ከመንግስት ጎን  ሆኖ ህገ ወጦችን እንዲያጋልጥ መልዕክት  ማስተላለፋቸውን ከታች አርማጭሆ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.