Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ፣ የደቡብና የአማራ ክልሎች በክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና እለፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ፣ የደቡብና የአማራ ክልሎች በክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና እለፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ ፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና እናትና አባት የሌላቸውን ወገኖች በመንከባከብና በማሳደግ በዓለም አቀፍና በሃገር አቀፍ ደረጃ ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ነው ያሉት፡፡
ለዚህና የሁሉም እናት ስለመሆናቸው ደግሞ ሁሉም ምስክር ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግስትም በህልፈታቸው ሲገልፅ ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅናም በመስጠት ጭምር መሆኑም በሃዘን መግለጫው ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የደቡብ ክልል መንግስት በክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን የገለፀ ሲሆን ዶክተር አበበች ለሰው ልጆች ካላቸው ጥልቅ ፍቅር እና ርህራሄ የበርካታ ዜጎች እናት ናቸው ብሏል።
እኒህ ታላቅ የሀገር ባለዉለታ በሰሩት የሰብአዊነት ተምሳሌት ህያዉ ስራቸው ምንግዜም ሲታወስ ይኖራል ሲል ገልጿል።
በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ላጡ ወገኖችን እናትም አባትም ሆነው ሰው ከወደቀበት ቀና እንዲል አድርገዋል ብለዋል።
በተመሳሳይ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል፡፡
እንደ አሚኮ ዘገባ “በሰብዓዊነታቸው ለተቸገረ ሰው በተለይም ለሕጻናት በሚያደርጉት ድጋፍ የሚታወቁት ዶክተር አበበች ጎበና ሕልፈተ ሕይወት የተሰማኝን ሐዘን በክልሉ መንግሥትና ሕዝብ እየገለጽኩ ፤ የእናታችን ነብስ በአፀደ ገነት ያኑርልን ዘንድ ፈጣሪን እለምናለሁ” ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ክልሎቹ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናት ተመኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.