Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ፡፡
የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ለዘላለም የሚኖሩ የደግነት ተምሳሌት ውድ እናት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበናን ማጣታችን አሳዛኝ ነው ብለዋል::
የጤና ሚኒስትር ወይዘሮ ሊያ ታደሰ ከ40 በላይ አመታት ህፃናትን በፍቅር በመንከባከብ እና ለቁምነገር በማብቃት የሚታወቁትና የብዙዎች እናት የነበሩት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው እጅግ ያሳዝናል ነው ያሉት።
ክብርት ዶክተር አበበች ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ከጎዳና እያነሱ አጥበው፣ አብልተው፣ አስተምረው በርካታ ልጆችን ለቁም ነገር ማብቃት የቻሉ ጀግና ሴት እንደነበሩ ያስታወሰው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለቤተሰቦቻቸው፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም የእርሳቸውን እንክብካቤ ለሚሹ ሕጻናት መጽናናትን ተመኝቷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.