Fana: At a Speed of Life!

ከክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ተግባር እኛም እንማር- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ፡፡
ፕሬዚዳንቷ ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ በደግነታቸውና ወደር በሌለው አዛኝነታቸው የሚታወቁት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበናን ዜና እረፍት በከፍተኛ ሀዘን ነው የሰማሁት ብለዋል፡፡
ክብርት ዶክተር አበበች የራሳቸው ልጅ ባይኖራቸውም በርካቶችን እንደ ራሳቸው ልጆች ማሳደጋቸውንም አንስተዋል፡፡
ከ1977 ድርቅ ሁለት ልጆችን በማሳደግ በጀመሩት የበጎ አድራጎት የተቀደሰ ተግባር ባለፉት 36 አመታት በርካታ ኢትዮጵያዊያንን አሳድገው ለቁም ነገር አብቅተዋል ፤ ከዚህም በመነሳት ከተግባራቸው እኛም እንማር ብለዋል ፕሬዚዳንቷ፡፡
በህልፈታቸውም ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለሰፊው ቤተሰባቸው መጽናናትን እመኛለሁ ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.