Fana: At a Speed of Life!

ለኤችአይቪ ሕሙማን የሚሆን አዲስ የቲቢ መመርመሪያ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኤችአይቪ ሕሙማን የሚሆን አዲስ የቲቢ መመርመሪያ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል፡፡

መመርመሪያውን ወደ ስራ እያስገቡ ያሉት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የጤና ሚኒስቴር ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር ነው።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኤችአይቪ ቲቢ ድርብ ጫና ካለባቸው 30 የዓለም ሀገራት አንዷ መሆኗ እና አዲሱ የመመርመሪያ ዘዴም ከዚህ ቀደም ከነበረው ውጤታማነቱ ከፍ ያለ እንደሆነ ተገልጿል።

አዲሱ የመመርመሪያ ዘዴ ከክልል የጤና ተቋማት ጋር በመሆን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች እንደሚተገበር ተገልጿል።

TB LF-LAM የተባለውና በሽንት ናሙና ላይ የሚደረገው ይህ ምርመራ  ጫናን ያቃልላል መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.