Fana: At a Speed of Life!

ግድቡ የኢትዮጵያን የሀይል ችግር የሚፈታ፣ የሱዳንና የግብጽን ስጋት የሚቀንስ ነው -ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የምንከተለው ሂደት የኢትዮጵያን የሀይል ችግር የሚፈታ፣ የሱዳን እና የግብጽን ስጋት የሚቀንስ እንዲሁም በጋራ የምናድግበት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
በምላሻቸው “በቀጠናው ሰላምና ብልጽግናን የሚያመጣ፣ ኃይል ሲመረት በጋራ የምንጠቀምበት፣ የውሃም ችግር ካለ እየተወያየን የምንፈታበት፣ ሰላማዊ የልማት ጉዞ እንዲሆን እንፈልጋለን፤ ለዚህም እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል፡፡
ሃገራትም ኢትዮጵያ ሌሎችን የመጉዳት ፍላጎት ሳይሆን በትብብር የማደግ ፍላጎት እንዳላት ተገንዝበው ጉዳዩ ቶሎ ተቋጭቶ ወደ አዳዲስ ልማቶች ለመሄድ ማገዝ እንደሚገባቸውም አውስተዋል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩም ዛፍ በመትከልና ዝናብ በማብዛት የውሃ ብክነትን በመቀነስ ራስን በመጥቀም ሌሎችም እንዲጠቀሙ ይደረጋልም ነው ያሉት፡፡
ሰላምና እድገትን ለማምጣትም በትብብር እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩልም ጎንደር፣ ደሴ፣ ነቀምትና በሌሎች ዋና ዋና ከተሞች የዳቦ ፋብሪካ ይገነባል ያሉ ሲሆን ይህም ሰው እንዳይቸገርና ዳቦ ገስቶ መብላት እንዲችል ያደርጋል ብለዋል፡፡
መሰል ተግባራት ሲስፋፉም ችግሩ እየቀነሰ ይሄዳል ነው ያሉት በምላሻቸው፡፡
“ስንዴ የሚለምን ህዝብ ክብር የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አርሰን ምርት ማግኘት አለብን ክብራችንን መመለስ አለብን” ብለዋል፡፡
በተያያዘውም የበጀት ዓመቱ አፈፃፀም ተጠቃሎ ባይደርስም 264 ቢሊየን ብር ገቢ ለማድረግ ታቅዶ 259 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዚህም 98 በቶ አፈፃፀም ማሳየቱን በመጥቀስ ከዓምናው አንፃርም እድገት አሳይቷል ነገር ግን አሁንም መሻሻል እንዳለበት አንስተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.