Fana: At a Speed of Life!

የ2014 የፌዴራል መንግስት በጀት 561 ነጥብ 67 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2014 በጀት ዓመት የቀረበውን 561 ነጥብ 67 ቢሊየን ብር በጀት አጸደቀ፡፡

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ ልዩ ስብሰባ በጀቱን አጽድቆታል።

በስብሰባው ላይ በፌዴራል መንግስት በጀት ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

በ2014 በጀት ዓመት ለሚከናወኑ ሥራዎችና አገልግሎቶች የሚያስፈልገውን ለፌዴራል መንግሥት መደበኛ ወጪዎች 162 ነጥብ 17 ቢሊየን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎች 183 ነጥብ 55 ቢሊየን ብር ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ 203 ነጥብ 95 ቢሊየን እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ 12 ቢሊየን ብር በድምሩ 561 ነጥብ 67 ቢሊየን እንደሆነ ነው ያብራሩት፡፡

የ2014 በጀትም አምራችነትን ለማሳደር የሚያግዝና ከ10 ዓመቱ መሪ እቅድ ጋር የሚጣጣሙ የኮሮና ቫይረስ የሚያስከትለውን ችግር ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.