ዓለምአቀፋዊ ዜና

ግብጽ የስዊዝ ካናልን ዘግታ የቆየችውን መርከብ ለመልቀቅ ተስማማች

By Tibebu Kebede

July 05, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መርከቧ ላደረሰችው ጉዳት ካሳ እስከሚከፈል ድረስ እንዳትንቀሳቀስ ታግዳ ቆይታለች፡፡

ከመርከቧ ባለቤቶችና ከመድህን ኩባንያው ጋር በተደረሰው የካሳ ስምምነት መሰረት ነው ግብጽ ኤቨር ግሪን የተባለችውን መርከብ እንደምትለቅ ያስታወቀችው፡፡

መርከቧ ስዊዝ ካናልን ዘግታ በቆየችባቸው ቀናት ለደረሰው ኪሳራ ግብጽ 550 ሚሊየን ዶላር ካሳ መጠየቋን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

እስካሁን ድረስ ከስምምነት የተደረሰበት የካሳ ክፍያ መጠን ይፋ አልተደረገም፡፡

የሜዲትራንያን ባህርን ከቀይ ባህር የሚያገናኘው ስዊዝ ካናል ተዘግቶ የቆየባቸው ስድስት ቀናት በዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ከስዊዝ ካናል ለቃ ከወጣች በኋላም በግሬት ቢተር ሃይቅ እንድትቆይ ተደርጓል፡፡

መርከቧ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ተለቆ ወደ መደበኛ ስራዋ ትገባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!