Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በዚህ ሳምንት የተጠቃለለ የምርጫ ውጤት እንደሚያሳውቅ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ሳምንት የተጠቃለለ የምርጫ ውጤት እንደሚያሳውቅ ገለጸ።

ድምጽ በተሰጠባቸው ሁሉም የምርጫ ክልሎች ውጤት ተጠቃሎ መግባቱን የቦርዱ የኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ለቦርዱ ያልደረሱ 30 የምርጫ ውጤቶች አሁን ላይ ተጠቃለው መድረሳቸውን ጠቅሰው፥ ቦርዱም በዚህ ሳምንት የተጠቃለለ የምርጫ ውጤት እንደሚያሳውቅ ገልጸዋል።

ተቋርጦ የነበረው የቁጫ ምርጫ ክልል የድምጽ ቆጠራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባሉበት በአዲስ አበባ ቆጠራው እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በነገሌ የምርጫ ክልል ድምፅ ባልተሰጠባቸው 30 የምርጫ ጣቢያዎች በቀጣይ ሀሙስ ድምጽ ይሰጣል ተብሏል።

በመግለጫው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተወዳደሩበት ኦሮሚያ ክልል ጎማ ቁጥር 2 የምርጫ ክልል በሰፊ ልዩነት ማሸነፋቸው ተጠቅሷል፡፡

በምርጫው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 76 ሺህ 892 ድምጽ ሲያገኙ የእርሳቸው ተፎካካሪ የሆኑት እጩ ደግሞ 236 ድምጽ አግኝተዋል ነው የተባለው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.