Fana: At a Speed of Life!

በጁባ የሚገኘው የ15ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን ጁባ የሚገኘው የ15ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት በግዳጅ ቀጠናቸው አካባቢ ለሚገኙ አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ ድገፍ አደረጉ፡፡
አባላቱ ከዕለት ጎርሳቸው በመቀነሰ ከጁባ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኮር ዌሰት በምትባል መንደር ለሚገኙ አቅም ደካማ አረጋዊያን አካል ጉዳተኞች ፣ሴቶች እና ህፃናት ነው ድጋፉን ያደረጉት።
በዚህም ድጋፍ ሩዝ፣ ቦሎቄ፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ፓስታ እንዲሁም ብርድ ልብስ እና አንሶላ በመስጠት አጋርነታቸውን አስመስክረዋል፡፡
በተጨማሪም የሻላቃው የህከምና ቡድንም አለም አቀፍ ወረርሸኝ የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሸኝ መንስኤ እና የመከላከያ መንገዶችን በማስተማር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን እንዲሁም ሳኒታይዘሮችን አድለዋል፡፡

በድገፍ አሰጣጥ ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የሻለቃው ምክትል  አዛዥ ለአስተዳዳር ሌተናል ኮሎኔል ጠይቅ  ዘመን ÷ ድጋፉ ከአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር  በመነጋገር በችግር የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማገዝ አላማ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል ።

በቀጣይም የአከባቢውን ህብረተሰብ በሚጠቅም ማናቸውም ጉዳዩች ላይ በመሳተፍ ወዳጅነታችንን እና አጋርነታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
በተረጂዎች ስም ድጋፉን በመቀበል ንግግር ያደርጉት የኮር ዌሰት ቀበሌ አስተዳዳር ጆን ሙጅሽ ማኩር በበኩላቸው ÷ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል አባላት ከዚህ ቀደምም መሰል ድጋፎችን ያደረጉላቸው ስለመሆኑ ገልጸዋል።
በ15ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ለተደረገላቸው ድጋፍም በማህበረሰቡ ስም ያላቸውን አድናቆት እና ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ድጋፍ ከተደረገላቸው የመንደሩ ኑዋሪዎች መካከል የ3 ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮሮማጄሬት ጆሴፍ በሰጡት አስተያየት ÷ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ይህን አይነቱን እርዳታ ማድረጉ ከልብ የሚያስመሰግን መሆኑን ገልፀው ፣ ከኮሮና ጋር በተያያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጣቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትም መደሰታቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.