Fana: At a Speed of Life!

ከ58 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው ሳምንት 58 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡

የኮንትሮባድ ዕቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደ ሃገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

ዕቃዎቹ የገቢ ኮንትሮባንድ 54 ሚሊየን 20 ሺህ 270ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ሲሆን ÷ ወጪ ደግሞ 4 ሚሊየን 824 ሺህ 957 ብር ግምት እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

ከተያዙት ኮንትሮባንድ ቁሶች መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ እና መድሃኒቶች ይገኙበታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 19 ተሽከርካሪዎች በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.